Fana: At a Speed of Life!

በሶማሊያ የተከሰተው ድርቅ የ43 ሺህ ሰዎች ሕይወት ቀጥፏል – ጥናት

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሊያ አሁንም የቀጠለው ድርቅ ባለፈው ዓመት ብቻ የ43 ሺህ ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉን ጥናት አመላከተ፡፡

በድርቁ ሳቢያ ሕይወታቸውን ካጡ ሰዎች ግማሽ ያኅሉ ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች መሆኑን በእንግሊዝ የሚገኘው የለንደን የትሮፒካል ሕክምና ትምህርት ቤት ጥናት አመላክቷል፡፡

በሶማሊያ አምሥት ተከታታይ የዝናብ ወቅቶች ዝናብ ሳያገኙ ማለፋቸውን ዘ ኢስት አፍሪካ አስታውሶ ዘግቧል፡፡

ድርቁ በርትቶ ከ17 ሚሊየን ሶማሌያውያን ግማሽ ያኅሉ ለአስቸኳይ ዕርዳታ እጃቸውን መዘርጋታቸውንም የተመድ መረጃ ያመላክታል፡፡

በፈረንጆቹ 2023 የመጀመሪያ 6 ወራት የሟቾች ቁጥር ከፍ ሊል እንደሚችልም ጥናቱ አመላክቷል፡፡

በአሁኑ ጊዜ 100 ሺህ የሚጠጉ ሶማሊያውያን ሥደተኞች በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ዶሎ ዞን ሰፍረው አስፈላጊውን የጤና አገልግሎት እና ሰብዓዊ ድጋፍ እያገኙ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት እና የኢትዮጵያ መንግስት መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.