Fana: At a Speed of Life!

የሆድ ድርቀትን መከላከያ ዘዴ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሆድ ድርቀት ህመም በአብዛኛው በአመጋገብ ለውጥ እና በበቂ ሁኔታ በፋይበር የበለጸጉ ምግቦችን ባለመመገብ ይከሰታል፡፡

በዕድሜ ገፋ ያሉ፣ ሴቶች፣ በቂ የሆነ በፋይበር የበለጸገ ምግብ የማይመገቡ፣ ለተለያየ ህመም መድኃኒት የሚወስዱ፣ የአንጎል እና የአከርካሪ አጥንት ህመም ያለባቸው ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ ለሆድ ድርቀት ተጋላጭ ናቸው፡፡

የሆድ ድርቀት የፊንጢጣ አካባቢ እብጠት፣ የፊንጢጣ መሰንጠቅ እና ሽንት አለመቆጣጠርን ያስከትላል፡፡

ከሦስት ሳምንታት በላይ የቆየ የሆድ ድርቀት ህመም ካጋጠመ እና በሰገራ ላይ ደም ከታየ የጤና ባለሙያ ማማከር ይገባል፡፡

በፋይበር የበለጸገ ምግብ አለመመገብ፣ በቂ ውሃ አለመጠጣት፣ በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ ከመጠን ያለፈ ወተት እና አይብ መመገብ ፣ ለተለያየ ህመም የሚወሰዱ መድኃኒቶች እና እርግዝና ለሆድ ድርቀት ህመም አጋላጭ መንስኤዎች ናቸው፡፡

ከሆድ ድርቀት ህመም ምልክቶች መካከል÷ የሰገራ መድረቅ ና ጠንካራ መሆን፣ በሰገራው ድርቀትና ጥንካሬ ምክንያት በአንጀት ላይ የህመም ስሜት መኖር እንዲሁም የሆድ ቁርጠት የሚሉት ይጠቀሳሉ፡፡

በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን ማዘውተር፣ አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ስንዴ፣ ጥራጥሬ ፣ ቴምር መመገብ፣ በቂ ፈሳሽ መውሰድ (ቡና እና አልኮል መቀነስ)፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የሆድ ድርቀትን ለማስታገስ ያግዛሉ፡፡

በተጨማሪም የሆድ ድርቀትን ለመከላከል÷ በሰዓቱ መመገብ፣ ቅባት እና ጣፋጭ የበዛበትን ምግብ አለመመገብ እንደሚመከር የሄልዝ ላይን መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.