Fana: At a Speed of Life!

የአካባቢ ጉዳይ ሳይንቲስት ዶ/ር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር የቀብር ስነ ስርዓት ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአካባቢ ጉዳይ ሳይንቲስት ዶክተር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።

በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል፡፡

ዶ/ር ተወልደ ብርሃን የተወለዱት ከአባታቸው ከቄስ ገብረ እግዚአብሔር ዮሐንስ እና ከእናታቸው ወይዘሮ መዓዛ ወልደ መድህን የካቲት 12 ቀን 1932 ዓ.ም በትግራይ ክልል ዓድዋ ከተማ አቅራቢያ ባለች “አዲ-ሰላም” የገጠር መንደር ነው።

በብዝሃ ሕይወት ጥናትና ምርምር ለሀገራቸውና ለዓለም የሚጠቅም አስተዋጽኦ በማበርከታቸው በርካታ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችንም አግኝተዋል።

በአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ ላደረጉት ምርምር በፈረንጆቹ 2000 “ራይት ላይቭሊሁድ አዋርድ” እና በፈረንጆቹ በ2006 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ ሰዎች የሚሰጠውን “ቻምፒዮንስ ኦፍ ዘ ኧርዝ” ካገኟቸው ሽልማቶች መካከል ይጠቀሳሉ።

ታዋቂው የአካባቢ ጉዳይ ሳይንስቲስት የዶክተር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት ሕይወታቸው ማለፉ ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.