Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ሲካሄድ የቆየው የከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ውይይት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም በአማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ደቡብ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ ሶማሌ፣ ሐረሪ፣ ሲዳማ እና ጋምቤላ ክልሎች በሀገራዊና ክልላዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ውይይት ተጠቀቀ፡፡

ውይይቱ÷ አመራሩ የተገኙ ስኬቶችንና ድሎችን ከማጽናት ባለፈ፣ ወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ፈተናዎችን በአግባቡ ተገንዝቦ የሚጠበቅበትን እንዲወጣ ለማድረግ ያለመመሆኑ ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን የሚዳስሱ፣ የተገኙ ስኬቶችን እንዴት ማጽናት እንደሚቻልና ፈተናዎችን ለመሻገር የቀጣይ አቅጣጫዎች ምን መሆን እንዳለባቸው ምክክር መደረጉን ከየክልሎቹ ኮሙኒኬሽን ቢሮዎች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ውይይቶቹ “ድሎችን የማጽናትና ፈተናዎችን የመሻገር ወቅታዊና ታሪካዊ አመራሮች ተልዕኮ” በሚል መሪ ቃል ነው የተካሄዱት፡፡

መድረኮቹ÷ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሠሞኑን ባካሄደው ውይይት ያሣለፋቸውን ውሣኔዎች፣ በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረጉ ነበሩ፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.