Fana: At a Speed of Life!

የዘንድሮ የሐጅ ተጓዦች 315 ሺህ ብር እንዲከፍሉ ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮ የሐጅ ተጓዦች 315 ሺህ ብር እንዲከፍሉ መተመኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ1444/2015 የሐጅ ጉዞን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

ምክር ቤቱ በመግለጫው ÷ የዘንድሮ የሐጅ ተጓዦች 315 ሺህ ብር እንዲከፍሉ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

ቀድሞ በፌደራል ጠቅላይ ምክር ቤቱ ብቻ ይሰጥ የነበረው የምዝገባ አገልግሎት በዘንድሮው የሐጅ ጉዞ መስተንግዶ ወደ ሐጃጁ በማቅረብ ምዝገባውን በ16 ጣቢያዎች በየአካባቢው እንደሚከናወን ተገልጿል።

በሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት እግድ የተጣለባቸው ዜጎች መመዝገብ እንደማይችሉም በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

በፈቲያ አብደላ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.