Fana: At a Speed of Life!

በብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን  ስራዎች ዙሪያ ከዓለም አቀፍ  አጋር አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ከዓለም አቀፍ አጋር አካላት ጋር የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ አካሂዷል፡፡

በመድኩ የተሃድሶ ኮሚሽን ከሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ፣  የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ሰመሪታ ሰዋሰው፣ በተመድ የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ካትሪን ሶዚ እና የተመድ የልማት ፕሮግራም ተወካይ ሚስተር ቱርሃን ሳሌህ ተገኝተዋል፡፡

የቀድሞው ተዋጊዎች በሰላማዊ መንገድ  ወደ ህብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ለማድረግ በማለም የሚደረገው የውይይት መድረክ ቀደም ሲል በመቀሌ መካሄዱ ይታወሳል፡፡

በቀጣይም በባህር ዳር፣ ሰመራ እና ሌሎች ከተሞች ላይ  እንደሚካሄድ ነው የተገለጸው፡፡

በውይይቱ የኢትዮጵያ መንግስት በግጭት የተጎዱ አከባቢዎችን መልሶ ለመገንባት እና የተፈናቀሉ ዜጎችን የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ ለማድረግ የሃብት ማሰባበሰብ ስራዎችን በተቀናጀ መልኩ እያከናወነ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ዘላቂ ሰላምን እና ልማትን ለማስፈን የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ እንዲፈቱ በማድረግ እና የተሃድሶ ስልጠና በመስጠት ወደ ህብረተሰቡ የመቀላቀል ስራ እየተከናወነ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስትን ጥያቄ ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የቁሳቁስ ድጋፍ እያደረገ ነው መባሉን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.