Fana: At a Speed of Life!

የጦር መሳሪያ በሕገ ወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ በተያዙ 10 ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተጣራ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ የጦር መሣሪያዎችን በሕገ ወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ ከእነኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር በዋሉ አሥር ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተጣራ መሆኑን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ወደ ኢትዮጵያ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ በማስገባት ላይ የነበሩ አራት ተጠርጣሪዎች ከእነኤግዚቢቱ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስ ገልጿል፡

ተጠርጣሪዎቹ÷ ብሬን፣ ክላሽንኮቭ እና መሰል ጥይቶችን በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ሐመር ወረዳ የኦሞ ወንዝን በጀልባ በማሻገር በሞተር ሳይክል እየጫኑ እንዳሉ ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ማዕከላዊ ወንጀል ኢንተለጀንስ፣ ከአካባቢው ፖሊስና ሕብረተሰብ ጋር በትብብር ባካሄደው ዘመቻ በቁጥጥ ስር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

በሌላ በኩል በአማራ ክልል የተለያዩ ሽጉጦች፣ 9 ክላሽንኮቭ፣ 13 ቦምቦችና የተለያዩ ጥይቶችን በሕገ ወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ሥድስት ተጠርጣሪዎች ከእነኤግዚቢቱ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.