Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ተማሪዎች በቤታቸው ሆነው በቴሌቪዥን እንዲማሩ ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ በኮሮና ቫይረሰ የተቋረጠወን ትምህርት በቴሌቪዥን ለማስጀመር ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለፀ።

የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ የቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አዲሱ ሻንቆ ለፋና ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩ፥ የቴሌቪዥን ትምህርት የሙከራ ስርጭት ሚያዚያ 7 2012 ዓ.ም በአፍሪ ሄልዝ የቴሌቪዥን የሚጀምር መሆኑን ገልፀዋል።

ለዚህም የመምህራን ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁንም አስታውቀዋል።

የግል ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችም በቴሌቪዥን በሚተላለፈው የትምህርት መርሃ ግብር እንደሚካተቱም አቶ አዲሱ ገልፀዋል።

በዚህም መሰረት ተማሪዎች በኤፍ ኤም 94 ነጥብ 7 እንዲሁም በአፍሪ ሄልዝ የቴሌቪዥን ጣቢያ የሚሰራጩ የትምህርት ፕሮግራሞች ተማሪዎች አቤት ቁጭ ብለው ሊከታተሉ ይገባል ነው ያሉት።

የ7ኛ እና 8ኛ እንዲሁም 9ኛ እሰከ 12ኛ ክፍል የሒሳብ የእንግሊዘኛ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት እንዲሁም የ11ኛ እና12ኛ ክፍል የታሪክ “ትምህርት በቤቴ” በሚለው ፕሮግራም በሬዲዮ እና በቴሌቪዥን እንዲከታተሉም አሳስበዋል።

ከ5ኛ እሰከ 8ኛ ክፍል ትምህርት በኤፍ ኤም 94 ነጥብ 7 ሬዲዮ ጣቢያ እየተላለፈ መሆኑን ያስታወሱት አቶ አዲሱ፥ ወላጆች በተለይ ተማሪዎች የመማሪያ መጽሀፍት በእጃቸው ላይ ስላለ ትምህርታቸው ላይ ትኩረት በማድረግ እንዲከታተሉ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

ብሔራዊ ሀገር አቀፈ ፈተናዎችን በተመለከተ ለኮሮና ቨይረሰ የታወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ የሚፈጸም እንደሆነ አቶ አዲሱ አስታወቀዋል።

የከተማ አሰተዳደር የራሱ የቴሌቪዥን ጣቢያ እያለው ለምን በሌላ ቴሌቪዥን እንዲሰራጭ ተፈለገ ለሚለው ጥያቄ አቶ አዲሱ፥ የከተማ አሰተዳደሩ ቴሌቪዥንና የሬዲዮ ጣቢያዎች በወቅታዊ የኮሮና ወረርሽኝ ስራ የበዛባቸው በመሆኑና አፍሪ ሄልዝ ቴልቪዥን በነፃ ለማስተላለፍ ፍቃደኛ በመሆኑ ነው ብለዋል።

የኮሮና በቫይረስ ከተከሰተ ጀምሮ መንግስት ከወሰዳቸው የቫይረሱን ሰርጭች ለመቆጣጠር ከወሰዳቸው እርምጃዎች ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው ትምህርት ቤቶችን መዝጋት እንደሆነ ይታወቃል።

በሲሳይ ጌትነት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.