Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ዣዎ ዥዩዋን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአፍሪካ – ቻይና ግንኙነት ላበረከተው አስተዋጽኦ አመሰገኑ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣዎ ዥዩዋን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቻይና እና አፍሪካን ግንኙነት በማጠናከር ረገድ ላበረከተው አስተዋፅኦ ምስጋና አቀረቡ፡፡

አምባሳደሩ በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቻይና ወደ ኢትዮጵያ በየሳምንቱ ከ50 ጊዜ በላይ በረራ እንደሚያደርግ በመረዳታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል፡፡

አየር መንገዱ በቻይና እና አፍሪካ የህዝብ ለህዝብ እና የንግድ ግንኙነት እያበረከተ ላለው አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.