Fana: At a Speed of Life!

ኮቪድ19ን የመከላከል ሥራው በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ዐውቄያለሁ- ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የኮሮናቫይረስ ኮቪድ19ን ለመከላከል ከተቋቋመው የሚኒስቴሮች ኮሚቴ ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው እንዳስታወቁት፥ “ኮቪድ19ን ለመከላከል ከተቋቋመው የሚኒስቴሮች ኮሚቴ ባደረክሁት ውይይት ቫይረሱን የመከላከል ሥራው በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ዐውቄያለሁ” ብለዋል።

የመጨረሻው አስከፊ ሁኔታ ቢከሠት ለመቋቋም ያስችል ዘንድ፣ በአዲስ አበባ ብቻ 1200 ያህል የምግብ መቀበያ ባንኮች መዘጋጀታቸውን በመስማታቸው እንዳስደሰታቸውም ገልፀዋል።

በክልሎችም፣ በየዕለቱ ምርመራውን ለማካሄድ የሚያስችሉ የመመርመሪያ ላቦራቶሪዎች እየተዘጋጁ መሆኑን እንዲሁም ለይቶ ለመከታተያ፣ ለይቶ ለማቆያ እና ለሕክምና የሚሆኑ ተጨማሪ ተቋማት በመዘጋጀት ላይ ናቸው ብለዋል።

የመተንፈሻ ቬንትሌተሮችን በኢትዮጵያ ለማምረት የሚቻልበት መንገድ እየተፈለገ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ፥ “በየአቅጣጫው የልግስና እጃችሁን የዘረጋችሁትን ደጋግ ወገኖችን ለማመስገን እወዳለሁ” ሲሉም መልእክት አስተላልፈዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.