Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ከወራት በፊት በእሳት ቃጠሎ በወደሙ ቤቶች ምትክ በአዲስ መልክ የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች ለነዋሪዎች ተሰጡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከወራት በፊት በአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማእከል ጀርባ በእሳት ቃጠሎ ወድመው በነበሩ ቤቶች ምትክ በአዲስ መልክ የተገነቡትን መኖሪያ ቤቶች ለነዋሪዎቹ አስረከቡ።

በወቅቱ ቃጠሎ የደረሰባቸው የ17 አባወራዎች ቤት ሲሆኑ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ባለሀብቶችን በማስተባበር በተሻለ መልኩ ገንብተው እንደሚያስረክቧቸው ቃል ገብተው ነበር።

ለነዋሪዎቹ የተገነቡት ቤቶች ባለ አንድ ፎቅ የሆኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሲሆኑ፥ የጋራ መኖረያ ቤቶቹ በባለሀብቶች ድጋፍ በ5 ወር ጊዜ ተሰርተው መጠናቀቃቸው ተገልጿል።

ቦታው ለኑሮ አመቺ አለመሆኑንና የሌሎቹ ነዋሪዎች ጥያቄን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ለሌሎቹ በአካባቢው ላሉ ነዋሪዎችም የዚህን መሰል መኖሪያ ቤቶች እንዲገነባ እንደሚደረግ ምክትል ከንቲባው ገልጸዋል።

ኢንጂነር ታከለ ኡማ አያይዘውም በቤቶቹ ግንባታ ላይ ለተሳተፉ ባለሀብቶችና የተለያዩ አካላት ምስጋና ማቅረባቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://t.me/fanatelevision

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.