Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶጋን ጋር በስልክ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶጋን ጋር በስልክ ተወያዩ።

ውይይቱን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው እንዳስታወቁት፥ “የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶጋን ኢትዮጵያ የኮቪድ19ን ፈተናዎች እንድትቋቋም ለማገዝ ፈቃደኛ ስለ ሆኑ ደስ ብሎኛል” ብለዋል።

“ለተሳካው የስልክ ውይይት ምስጋናዬን እያቀረብሁ፤ እጅግ ተፈላጊ የሆኑትን የሕክምና መገልገያዎች በሚያቀርቡበት ሂደት አብሬዎት እሰራለሁ” ሲሉም ገልፀዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.