Fana: At a Speed of Life!

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት የኩፍኝ በሽታ ዳግም እንዳይከሰት ያሰጋል – ተመድ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኩፍኝ በሽታ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ዳግም ሊከሰት እንደሚችል ስጋት መኖሩን የተባበሩት መንግስታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት ገለጸ።

ስጋቱ የመጣው በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት አንዳንድ የክትባት ፕሮግራሞች በመዘግየታቸው መሆኑ ነው የተገለጸው።

በዚህም በ37 አገሮች ውስጥ 117 ሚሊዮን ሕፃናት በወቅቱ ክትባት ሊወስዱ እንደማይችሉ የድርጅቱ ሀላፊዎች ጠቁመዋል።

በአሁኑ ወቅት ገዳይ ሊሆኑ የሚችሉ ኢንፌክሽኖች እየጨመሩ በመሄዳቸው ምክንያት እንግሊዝ ከኩፍኝ በሽታ ነፃ ሀገር የሚለውን ስሟን ማጣቷም ነው የተነገረው።

ጉንፋን፣ ሽፍታ እና ትኩሳትን የሚያስከተለው የኩፍኝ በሽታ በከፍተኛ ደረጃ ተላላፊ እንደመሆኑ በክትባት በቀላሉ መከላከል ይቻላልም ነው የተባለው።

በመሆኑም የክትባቱ ስርጭት ዝቅተኛ በሆነባቸው የአውሮፓ ሀገራት የሚገኙ ህጻናት በወረርሽኙ መጠቃታቸው ተነግሯል።

በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት 24 አገራት የኩፍኝ ክትባት ዘመቻዎቻቸውን ለማዘግየት ወስነዋልም።

የዩኔሴፍ ቃል አቀባይ ጆአና ረአ በመደበኛ ክትባት አገልግሎት ላይ የሚደረጉ መቋረጦች ሕፃናትን ለሞት በሚያጋልጡ በሽታዎች የመያዝ እድላቸውን ከፍ የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል።

ስለሆነም በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት ክትባቱን ማቆም አስቸጋሪ ምርጫ ከሆነ አመራሮችን ክትባቱን የማያገኙ ሕፃናትንና ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በመከታተል ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

አያይዘውም በአሁኑ ወቅት የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በብሔራዊ የጤና አገልግሎቶች ላይ ከሚያደርሰው ጫና በተጨማሪ ተላላፊ በሽታዎች ሁለተኛ ወረርሽኝ ሊያስከትሉ ይችላሉ ሲሉም ነው ያስጠነቀቁት።

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.