Fana: At a Speed of Life!

ጅቡቲ ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ለሚላኩ ዕቃዎች ለወደብ ከምትከፍለው ላይ 82 ነጥብ 5 በመቶ ቅናሽ ማድረጓን ጠ/ሚ ዐቢይ ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጅቡቲ ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ለሚላኩ ዕቃዎች ለወደብ ከምትከፍለው ላይ 82 ነጥብ 5 በመቶ ቅናሽ ማድረጓን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ፥ “የጅቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ ድጋፍ የሚያስፈልጋትን ጎረቤት ሀገራቸው ኢትዮጵያን በማሰባቸው እጅግ አመሰግናቸዋለሁ” ብለዋል።

እርምጃው በጋራ አመራር አማካኝነት የኮቪድ19ን ተጽዕኖ የመቋቋም ጥሩ ምሳሌ ነው ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አስታውቅዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.