Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የኮሮና ቫይረስ ተጋላጭነትን ለመቀነስ እና የተረጋጋ የበዓል ግብይት ማካሄድ የሚያስችሉ ቦታዎች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ ተጋላጭነትን ለመቀነስ እና የተረጋጋ የበዓል ግብይት ለማካሄድ የቁም እንስሳት መሸጫ ቦታዎች ዝርዝር ይፋ ሆነዋል።

የከተማው ንግድ እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ባወጣው መግለጫ ነጋዴው እና ሸማቹ በግብይቱ ወቅት ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ብሏል።

የገበያ ቦታዎቹም
1. አቃቂ ወረዳ 8 (የከብት በረት ማዕከል) ውስጥ ሲሆን ይህንን ለማስፋፋትም ወረዳ 8 ፊት ለፊት የሚገኘው ጥምቀተ ባህር ግቢ ውስጥ ግብይት ይፈጸማል፤

2. የካ ወረዳ 12 የነበረውን መገበያያ ወደ ወረዳ 1 በማዛወር ግብይቱ እንዲከናወን ይደረጋል፤

3. ኮልፌ ቀራኒዮ፡- በቀራኒዮ በኩል ወደ ቤቴል በሚወስደው መንገድ (ወረዳ 7) መንዲዳ የሚባል ቦታ ላይ ተዘጋጅቷል፤

ጉለሌ የነበረው ሸጎሌ የቁም እንስሳት መሸጫ ማዕከልን ለማስተንፈስ እንዲያስችል ወደዚህ ስፍራ እንዲዘዋወር ተደርጓል፤

4. ብርጭቆ ወረዳ 13 የነበረውን ደግሞ እዛው ወረዳ ላይ ሶስት ቦታ በማዘጋጀት – ኒኮላ ሜዳ፣ ሻወር ቤት ብርጭቆ አጠገብ ወረዳ 14 ኦሮሚያ ድንበር ላይ ልዩ ስሙ ኦሮሚያ ሜዳ የሚባል ቦታ ላይ ይከናወናል፤

5.ንፋስ ስልክ – ቄራ ከብት በረት ወረዳ 6 ላይ ያለውን በማስፋፋት ወረዳ 5 ላይ በተጨማሪነት እንዲገበያዩ ይደረጋል፤

6. በግና ፍየል ወረዳ 2፣ 3፣5፣ 10 ላይ እና (ቫርኔሮ አደባባይ) ለቡ ጀሞ አካባቢ ተዘጋጅተል፤

ነጋዴው እና ሸማቹም ማስክ እና የእጅ ጓንት መጠቀም፣ ከእንስሳቱ እና ከተለያዩ እቃዎች ጋር ንክኪን በጥንቃቄ በመተግበር እና ንፅህና መጠበቂያ ግብዓቶችን ማዘጋጀት እና መጠቀም እንዳለበትም ቢሮው አሳስቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.