Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የተከሰተውን የኢኮኖሚ ጫና ለመቋቋም የካርጎ አገልግሎት እያሰፋ መሆኑን ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 7 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ እየደረሰበት ያለውን የኢኮኖሚ ጫና ለመቋቋም ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች ለኮሮናቫይረስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ የሚደረጉ ጥንቃቄዎችን በማስመልከት መግለጫ ሰጥቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም ተቋሙ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ያጋጠመውን የኢኮኖሚ ጫና ለመቋቋም የተለያዩ ጥረቶችን እያደረገ ነው ብለዋል።

አየር መንገዱ የመንገደኞች አገልግሎት በረራውን በመቀነስ የካርጎ ጭነት አገልግሎቱን በማስፋት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የካርጎ አገልግሎቱም ከአፍሪካ በተጨማሪ በአውሮፓና ቻይና ጭምር ሰፊ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚ አስታውቀዋል።

አቶ ተወልደ አየር መንገዱ ቀደም ሲል የካርጎ ጭነት አገልግሎት ሲሰጡ ከነበሩት አውሮፕላኖች በተጨማሪ 8 የመንገደኛ ማጓጓዣ አውሮፕላኖችን ለካርጎ ስራ አሰማርቷል ብለዋል።

ሆኖም 90 የሚሆኑት የመንገደኛ ማጓጓዣ አውሮፕላኖች ስራ ፈትተው መቆማቸውን መገለፁን ኢዜአ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ በተስተጓጎለው በረራ የ550 ሚሊየን ዶላር ኪሳራ እንደገጠመው ማስታወቁ ይታወሳል።

አየር መንገዱን በሚመለከት አንዳንድ የተሳሳቱ መረጃዎች እንደሚናፈሱ የጠቆሙት አቶ ተወልደ የዱባይ በረራውን አላቋረጠም መባሉ ትክክል አለመሆኑን አስረድተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.