Fana: At a Speed of Life!

የቡድን 20 አባል ሀገራት የደሃ ሀገራትን የብድር መክፈያ ጊዜ አራዘሙ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 7 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የቡድን 20 አባል ሀገራት የደሃ ሀገራትን የብድር መክፈያ ጊዜ ማራዘማቸውን አስታውቀዋል።

የአባል ሀገራቱ የገንዘብ ሚኒስትሮች በዛሬው ዕለት ውይይት አድርገዋል።

በዚህም ሀገራቱ የደሃ ሀገራት የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመቆጣጠር እያደረጉት የሚገኘውን ጥረት ለመደገፍ የብድር መክፊያ ጊዜውን ለማራዘም ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

በስምምነቱ መሰረትም የብድር መክፈያ ጊዜው ከፈረንጆቹ ግንቦት 1 ቀን 2020 እስከ ዓመቱ መጨረሻ ይቆያል ተብሏል።

እንዲራዘም የተወሰነው ይህ ብድር የዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት አባል የሆኑ ደሃ ሀገራት ላይ ጫና የሚፈጥር ነበረ ነው የተባለው።

የአለም ባንክ እና የአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም ( አይ ኤም ኤፍ ) መሪዎችም ይህን ውሳኔ አድንቀዋል።

ምንጭ ፡-አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.