Fana: At a Speed of Life!

ፀሎተ ሀሙስ በተለያዩ ኃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች ታስቦ ዋለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፀሎተ ሀሙስ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በዛሬው እለት በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ታስቦ ውሏል።

የፀሎተ ሀሙስ በዓል በተለይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርሰቲያን እና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የኢየሱስ ክርስቶስ ትህትና በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ነው የተከበረው።

ክርስቶስ በዛሬዋ እለት የሃዋርያትን እግር ዝቅ ብሎ በማጠብ ትህትናን እና ታዛዥነት ማስተማሩን በማሰብ ነው በዓሉ ተከብሮ የዋለው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርሰቲያን በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል የፀሎተ ሀሙስ በዓል በተለያዩ ስነ ስርዓቶች አስቦ ውሏል ።

በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እየታከሄደ ባለው ምርሃ ግብር ላይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስን ጨምሮ ብፁዓን ጳጳሳት፣ ቆሞሳቱ፣ ካህናና ዲያቆናት ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሚካሄደው ስነ ስርዓትም ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ የብፁዓን ጳጳሳቱን፣ ብፁዓን ጳጳሳቱ ደግሞ ቆሞሳቱ እና ካህናቱ እግር በማጠብ የኢየሱስ ክረስቶስን አርአያነት ተከትለው ስርዓቱን ፈጽመዋል።

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንም የፀሎተ ሀሙስ በልደታ ማሪያም ካቶሊክ ካቴድራል በተለያዩ ኃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች አስበው ውለዋል።

በስነ ስርዓቱ ላይም የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌልን ጨምሮ የቤተክርስቲያኒቷ ካህናት በተገኙበት በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ታስቦ ውሏል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.