Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ አክሲዮን ማህበር የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት ድጋፉን እንደሚቀጥል አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ አክሲዮን ማህበር የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት ድጋፉን እንደሚቀጥል አስታወቀ።

ባንኩ በወረርሽኙ ለተጎዱ የህብረት ስራ ማህበራት፣ የሃገር ውስጥ ንግድ፣ የሆቴል ዘርፍ፣ አምራቾች፣ ግብርና፣ የተሸከርካሪ፣ ህንጻና ግንባታ፣ የገቢ ንግድ እና ቤትና የግል ብድሮች ላይ እስከ 5 በመቶ የሚደርስ የወለድ ቅነሳ ማድረጉን ነው ያስታወቀው።

በተመሳሳይ በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኩል የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚውል የ3 ሚሊዮን የገንዘብ ድጋፍ ሲያበረክት ነቀምቴ እና ኩዩ ከተማ የሚገኙ ሁለት ባለ7 ፎቅ ህንፃዎችን በጊዚያዊነት አበርክቷል።

በተጨማሪም ለባንኩ ሰራተኞች የተለያዩ ድጋፍና አማራጮችን በማቅረብ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት አስተዋጽዖ እያደረገ መሆኑን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ባንኩ ከዚህ ቀደም በጤና ሚኒስቴር በኩል የ5 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉም የሚታወስ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.