Fana: At a Speed of Life!

ዩክሬን ኔቶን መቀላቀል የለባትም ስትል አሜሪካ ተቃወመች

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)አንዳንድ የኔቶ አባል ሀገራት ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) እንድትቀላቀል የሚያደርጉትን ጥረት አሜሪካ ተቃወመች፡፡

ዩክሬን ኔቶን እንድትቀላቀል የሚሹ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅቱ አባል ሀገራት ግልፅ ያሉትን “አቅጣጫ” ሲያመላክቷት ቆይተዋል፡፡

የጆ ባይደን አስተዳደር የቃል-ኪዳኑ አባል ሀገራት እና አጋሮች ለኪዬቭ እያቀረቡ ያሉት ድጋፍ ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ አሳስቧል።

ከዚህ ጋር በተያያዘም አሜሪካ ኪዬቭን ወደ ቃል ኪዳኑ ከመቀላቀል የአጭር ጊዜ ድጋፍ ማድረጉ ይሻላል ማለቷን አር ቲ ዘግቧል።

በጉዳዩ ላይ ጀርመንና ሃንጋሪም ከአሜሪካ ጎን ሲሆኑ ፖላንድ እና የባልቲካ ሀገራት ግን ኪየቭ ኔቶን እንድትቀላቀል አጥብቀው ይሻሉ፡፡

ጉዳዩ በዚህ ሳምንት በብራስልስ በተካሄደው የኔቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ተነስቶ አከራክሮም ነበር።

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ዜሌንስኪ ÷ ሐምሌ ወር ላይ በሉቴኒያ ቪልኒየስ ከተማ በሚካሄደው ስብሰባ ላይ የሚካፈሉት ኪየቭ ኔቶን እንድትቀላቀል የሚያስችላትን እርምጃ የኔቶ አባል ሀገራት ከወሰዱ ብቻ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ዩክሬን አባል ሀገራቱ የደኅንነት ዋስትና እንደሚሰጧቸው እና ትብብራቸውን እንደማያቋርጡ እንዲያረጋግጡላቸውም ይፈልጋሉ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.