Fana: At a Speed of Life!

የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ የግብርናውን ዘርፍ በማሸጋጋር ረገድ ትልቅ ሚና እንዳለው ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢኮኖሚውን ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለማሸጋገር ትልቅ ሚና እንዳለው የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ተናገሩ፡፡

የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚኒስትሮች ኮሚቴ በተቀናጀ ግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ ዙሪያ ውይይት አካሄዷል::

የኮሚቴው ሰብሳቢ  አቶ መላኩ አለበል በውይይቱ እንደተናገሩት÷ የተቀናጀ የግብርና ኢንዱትሪ ፓርኮች በዋናነት የግብርናውን ዘርፍ በማሸጋጋር ረገድ ትልቅ ሚና አለው፡፡

እስካሁንም ከ140 ሺህ  በላይ ለሆኑ አርሶ አደሮች ማምረት ከጀመሩ ኢንዱስትሪዎች ጋር የገበያ ትስስር መፍጠር መቻሉን  ገልጸዋል፡፡

ይህም በምርት ጥራት እና መጠን እድገት ላይ  ከፍተኛ መሻሻል  አምጥቷል ያሉት  አቶ መላኩ ለዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ረገድም ትልቅ ሚና እንዳለው አመላክተዋል፡፡

እስካሁን ባለው ሂደትም ፓርኮቹን በተሟላ ቁመና ለባለሃብቶች ምቹ ለማድረግ በርካታ ስራዎች የተሰሩ ቢሆንም የመሰረተ ልማት ግንባታ፣ ፓርኮቹን የማስተዋወቅ እና የገጽታ ግንባታ  ስራዎች መስራት አንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

በውይይቱ የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ፣የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው፣የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ንጉሱ ጥላሁን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መሳተፋቸውን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.