Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ አመታዊ የጥናትና ምርምር አውደጥናት እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ” ችግር ፈቺና ምርምር ለከተማችን የላቀ ለውጥ ” በሚል መሪ ሀሳብ አመታዊ የጥናትና ምርምር አውደ ጥናት እያካሄደ ነው።

በአውደ ጥናቱ አካዳሚው በተለያዩ የመዲናዋ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ ያጠናቸውን የምርምር ውጤቶች አቅርቦ ምክክር እየተደረገባቸው ይገኛል።

የአዲስአበባ አመራር አካዳሚ ፕሬዚዳንት ደሳለኝ ጴጥሮስ (ዶ/ር) እንደገለፁት÷ አካዳሚው በመዲናዋ አመራሮችና ባለሙያዎች ላይ ለውጥ ማምጣት የሚችሉ ተፅዕኖ በመፍጠር የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው ብለዋል።

 

አካዳሚው እስካሁን ከ40 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የመዲናዋ አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠናዎችን ሰጥቶ ብቁ ማድረጉን የገለፁት ፕሬዚዳንቱ ከ35 በላይ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን መካሄዳቸውን ገልፀዋል።

በተጨማሪም አካዳሚው የመዲናዋ ተቋማት እርስ በርሳቸው ስትራቴጂካዊ ትስስሮችን እንዲፈጥሩና የልምድ ልውውጥ በማድረግ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ይሰራልም ነው ያሉት።

 

በአለምሰገድ አሳዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.