Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ በነፃነት ፀንታ ትቆያለች – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ጀግኖች ልጆች ስላሏት በነፃነት ፀንታ ትኖራለች ሲሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ስር የሚገኘው የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ ያሰለጠናቸውን ዕጩ መኮንኖች በሁርሶ የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ዛሬ አስመርቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ በምረቃ ሥነስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ኢትዮጵያ ጀግኖች ልጆች ስላሏት በነፃነት ፀንታ ትኖራለች ብለዋል።
ኢትዮጵያን የማበልፀግና የማፅናት ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።
ኢትዮጵያ ጀግኖች ስላሏት ሁሌም በነፃነትና በጀግንነት ትታያለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ተመራቂ መኮንኖችም የኢትዮጵያን አይበገሬነት የማፅናትና የማስቀጠል ኃላፊነትን በተግባር ማረጋገጥ እንዳለባቸው በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡
ተመራቂ መኮንኖቹ÷ ለምንም ነገር የማይቆሙ፣ ፈተና የሚያበረታቸው እንጂ ሸብረክ የማያደርጋቸው ሀገርን ወደ ተሻለ ደረጃ የሚያሻግሩ ሊሆኑ እንደሚገባም ነው መልዕክት ያስተላለፉት፡፡
ጀግና ማለት ለገባው ዓላማ እራሱን የሚሰጥ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ÷ ኢትዮጵያን ከነሙሉ ክብሯ ለትውልድ ለማስረከብ ዝግጁ መሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ውጊያን ጨምሮ በሁሉም ዘርፎች ለምርቃት የሚያበቃ ዝግጅትና ታላቅነትን በተግባር ያሳየንበት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚገኝበት “ጉባ” የሚለውን ስያሜን የያዛችሁ በመሆኑ ምርቃቱ ከዚህ ቀደም ከነበሩት ምረቃዎች ልዩ ያደርገዋል ብለዋል፡፡
ተመራቂ መኮንኖችም እራስን በእውቀት በማጎልበት፣ በመትጋት፣ በመማር፣ ዘመናዊነትን በመላበስ ለተሻለ ተግባር ራሳቸውን ለማዘጋጀት እንዲተጉ ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

 

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.