Fana: At a Speed of Life!

ኢራን በሳዑዲ ኤምባሲዋን ዳግም ለመክፈት የቴክኒክ ልዑክ ወደ ሪያድ ልትልክ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢራን በሳዑዲ ዓረቢያ ኤማባሲዋን ዳግም ስራ ለማስጀመር የቴክኒክ ልዑክ ወደ ሪያድ በተያዘው ሳምንት ልትልክ መሆኑን አስታውቃለች፡፡

ኢራን እና ሳዑዲ ዓረቢያ ከሰባት ዓመታት ባላንጣነት በኋላ በቻይና አሸማጋይነት ወደ ቀደመ ግንኙነታቸው ለመመለስ መስማማታቸው ይታወሳል፡፡

ባሳለፍነው ሐሙስ ዕለትም የሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በቻይና ቤጂንግ ከሳባት ዓመታት በኋላ መደበኛ ውይይት ማድረጋቸው ተጠቁሟል፡፡

ይህን ተከትሎም ኢራን በሳዑዲ ዓረቢያ ኤምባሲዋን ዳግም ለመክፈት የቴክኒክ ልዑክ ወደ ሪያድ በተያዘው ሳምንት እንደምትልክ አስታውቃለች፡፡

ልዑካኑ በቆይታቸውም ኤምባሲውን ዳግም ስራ ማስጀመር የሚያስችሉ በርካታ ስራዎችን ያከናውናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ቲ አር ቲ ዘግቧል፡፡

ከዚህ ባለፈም የሀገራቱን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ቀደመ ሁኔታው መመለስ የሚያስችል ውይይት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚያደርጉ ተመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.