Fana: At a Speed of Life!

ሊቢያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል  የ10 ቀናት የሰዓት እላፊ  አወጀች

አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 8፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሊቢያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ስርጭትን ለመከላከል ለ10 ቀናት  የሚቆይ   የ24 ሰዓት  እላፊ አወጀች፡፡

በተባበሩት መንግስታት  ድርጅት የሚደገፈው የሀገሪቱ  መንግስት ÷  ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያስችል ዘንድ ዜጎች ለ10 ቀናት ከቤታቸው እንዳይወጡ   አግዷል፡፡

ከዚያም ባለፈ በነዚህ ቀናት ሁሉም የአትክልት እና የስጋ ገበያዎች የሚዘጉ ሲሆን  ዳቦ መጋገሪያዎች እና አንዳንድ ሱቆች ክፍት እንደሚሆኑም ነው የተነገረው ፡፡

እገዳው አርብ እለት ይጀምራልም ነው የተባለው፡፡

በሊቢያ እስካሁን በኮቪድ -19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 48 ሲሆን አንድ ሰው ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ለህልፈት ተዳርጓል፡፡

በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2011 ሀገሪቱን ለረዥም አመታት የመሩት ሙአመር ጋዳፊ  ከተገደሉ ጀምሮ ሊቢያ በግጭት ውስጥ መውደቋ ይታወቃል ፡፡

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.