Fana: At a Speed of Life!

የቻይና የህክምና ባሉሙያዎች ኢትዮጵያ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ የተላኩ የቻይና የህክምና ባለሙያዎችን አዲስ አበባ ገብተዋል።

በውስጡ 12 ልኡካንን የያዘው የቻይና የህክምና ባለሙያዎች ቡድን በዛሬው እለት ነው አዲስ አበባ የገቡት።

የህክምና ባለሙያዎቹ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

እነዚህ የህክምና ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ቆይታቸው ልምዳቸውን የሚያጋሩ ሲሆን፥ በተጨማሪም የኮሮና ቫይረስን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የሚያስችሉ መመሪያዎችን እና ቴክኒካል ምክሮችን ለጤና ባለሙያዎች እና ለህክምና ተቋማት ያካፍላሉ ተብሏል።

ቻይና ከኢትዮጵያ በተጨማሪም የህክምና ባለሙያዎችን ወደ ቡርኪና ፋሶ መላኳም ይታወቃል።

የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዝሆ ሊጂዓን፥ ቻይና ከአፍሪካ ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንዳላት ከዚህ ቀደም መግለፃቸው ይታወሳል።

በአፍሪካ ቫይረሱን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር እየተከናወነ ያለውን ስራ ሀገራቸው እንደምትደግፍም ቃል አቀባዩ ገልፀዋል።

በአፍሪካ ሀገራት ያለውን ሁኔታ በትኩረት እየተከታተለች መሆኑን ያስታወቀችው ቻይና ቫይረሱን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የሚያስችሉ መሳሪያዎችን ማቅረቧም ይታወሳል።
በፀጋዬ ንጉስ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.