Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ በበልግ እርሻ ከ764 ሺህ ሔክታር መሬት በላይ በዘር ተሸፈነ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በበልግ እርሻ እስካሁን ከ764 ሺህ ሔክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

በኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ጌቱ ገመቹ የተመራ ልዑክ በምዕራብ ሐረርጌ ዞን የበልግ እርሻ እንቅስቃሴን ጎብኝቷል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት የቢሮ ኃላፊው እንደገለጹት÷ በክልሉ በበልግ እርሻ 1 ሚሊየን 122 ሺህ 789 ሔክታር መሬት ለማልማት ታቅዷል።

እስካሁንም ከ764 ሺህ 395 ሔክታር መሬት በላይ በዘር ተሸፍኗል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

በበልግ እርሻው ለውጭ ምርቶች ትኩረት መሰጠቱንም ነው ያመላከቱት፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.