Fana: At a Speed of Life!

የቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በዓለም ዙሪያ ለኮሮና ቫይረስ መከላከል የሚውል የ150 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ለመከላከል የሚውል የ150 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አደረገ።

የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን እንዳስታወቀው የገንዘብ ድጋፉ የቫይረሱን ወረርሽኝ ለመከላከል የሚያስችሉ መሰረታዊ ቁሳቁሶችን ለአፍሪካ እና ደቡብ እስያ ሀገራት ለማሟላት እና ኩባንያዎች መሰል መሳሪያዎችን እንዲያመርቱ ለማገዝ የሚውል ነው።

በተጨማሪም ቫይረሱን የሚከላከሉ መድሃኒቶችና ክትባትን ለማበልፀግ እንደሚውልም በመግለጫው ተመልክቷል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም ፋውንዴሽኑ ወረርሽኙን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ላደረገው ድጋፍ በትዊተር ገጻቸው ላይ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.