Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከኢስቶንያ አቻቸው ጋር ስለኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከኢስቶንያ ፕሬዚዳንት ከረስቲ ካልጁሌይድ ጋር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በሚደረጉ ጥረቶች ዙሪያ በስልክ ተወያይተዋል።

በውይይቱም የበሽታውን ስርጭትም ሆነ የሚያስከትላቸውን ጉዳቶች ለመቆጣጠር እንዲቻል የተቀናጀ አጋርነትን መፍጠር እንደሚገባ መሪዎቹ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

በዚሁ ወቅት ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በሀገር ደረጃ ስለተወሰዱ እርምጃዎች አብራርተው፤ ወረርሽኙን ለመከላከል በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለመጠቀም እንቅስቃሴ በመጀመሩ አንስተዋል።

ፕሬዚዳንቷ አያይዘውም ኢስቶንያ በዚህ ዘርፍ ካተረፈችው እውቅና አንጻር በሽታውን በመከላከል ሂደት ካላት ተሞክሮ ለመጠቀም ኢትዮጵያ  እንደምትሻ ገልጸዋል።

በዚህም የሚመለከታቸው አካላት በቶሎ እንዲገናኙ  መስማማታቸው ተገልጿል።

የኢስቶንያ ፕሬዚዳንት ከረስቲ ካልጁሌይድ በበኩላቸው፥ በኢትዮጵያ ሴት የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞችን በማሰማራት ቫይረሱ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመከላከል የሚደረገውን ጥረትናየኢትዮጵያ አየር መንገድ የጤና ቁሳቁሶችን ለአፍሪካ አገሮች እያደረሰ መሆኑን አድንቀዋል።

ከዚያም ባለፈ ፕሬዚዳንት ካልጁሌይድ በሀገራቸው በኩል እየተወሰዱ ያሉና በአውሮፓና በዓለም አቀፍ ደረጃም እየተገበሩ ስላሉ እርምጃዎች ማብራራታቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.