Fana: At a Speed of Life!

የ1 ሺህ 444ኛው የ2015 የሐጅ መስተንግዶ ማብራሪያ እና የሐጅ ምዝገባ ሲስተም ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ1 ሺህ 444ኛው የ2015 የሐጅ መስተንግዶ ማብራሪያ እና የሐጅ ምዝገባ ሲስተም ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ፡፡

የዘንድሮው የሀጅ ጉዞ እንግልት አልባ እንዲሆን ታስቦ ሲስተሙ እውን መደረጉ ተገልጿል።

ሀጃጆቹ ባሉበት ሆነው እንዲመዘገቡ ከዘጠኝ ባንኮች ጋር ውል ተገብቷል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ኢብራሂም ቱፋ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት የዘንድሮው የሀጅ መስተንግዶ ሂደት ተዓማኒ እና ከእንግልት ነፃ እንዲሆን ጥረት ይደረጋል።

ከዛሬ ጀምሮም ሀጃጆች በዘጠኙ ባንኮች መመዝገብ እንደሚችሉ የተገለጸ ሲሆን፥ ሲስተሙ እውን እንዲሆን በሁሉም ዘርፍ ለተባበሩ ምስጋና ይድረስ ተብሏል።

በፈትያ አብደላ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.