አቶ ማሞ ምሕረቱ ከጣልያን ባንክ ምክትል ገዥ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምሕረቱ ከጣልያን ባንክ ምክትል ገዥ ፒዬሮ ሲፖሎንጋር ተወያዩ፡፡
ውይይቱን ያካሄዱት ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም እና የዓለም ባንክ የ2023 የፀደይ ወቅት ስብሰባ ጎን ለጎን ነው፡፡
በውይይታቸውም÷ በዘርፉ ያሉ አሠራሮችን ለማጎልበት የጣልያን ባንክ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በክፍያ ሥርዓት፣ ማክሮ እና ስታትስቲክስ ዙሪያ የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተስማምተዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምሕረቱ በትናንትናው ዕለትም÷ ከኬንያ፣ ዛምቢያ፣ ሞዛምቢክ እና ዩጋንዳ ማዕከላዊ ባንኮች ገዥዎች ጋር መወያየታቸው ይታወሳል፡፡