Fana: At a Speed of Life!

የጣና ሞገዶቹ ድሬዳዋ ከተማን ረቱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 19ኛ ሣምንት ጨዋታ ባሕርዳር ከተማ ድሬዳዋ ከተማን 3 ለ 1 አሸነፈ፡፡

ባሕዳር ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ 9፡00 ላይ በአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን አካሂደዋል፡፡

በዚህም ሀብታሙ ታደሠ በመጀመሪያው አጋማሽ ባስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች እና ዱሬሳ ሹቢሳ በሁለተኛው አጋማሽ ባስመዘገባት አንድ ጎል ባሕርዳር ከተማ ማሸነፍ ችሏል፡፡

የድሬዳዋ ከተማን ብቸኛ ጎል በሁለተኛው አጋማሽ ቢንያም ጌታቸው አስቆጥሯል፡፡

እንዲሁም ምሽት 12፡00 ላይ በተካሄደው የጨዋታ መርሐ ግብር ሀድያ ሆሳዕና አርባምንጭ ከተማን 2 ለ 0 ረትቷል፡፡

ጎሎቹንም ፍቅረየሱስ ተ/ብርሃን በመጀመሪያው አጋማሽ እና ፀጋዬ ብርሃኑ በሁለተኛው አጋማሽ አስቆጥረዋል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.