Fana: At a Speed of Life!

ዶክተር ሊያ ታደሰ ለቻይና የህክምና ባሉሙያዎች ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ የተላኩ የቻይና የህክምና ባለሙያዎችን ቡድን አመሰገኑ።

ዶክተር ሊያ በፌስ ቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ የህክምና ባሉሙያዎቹ በወረርሽኙ ቁጥጥር ላይ ያላቸውን የዳበረ ልምድ በማካፈል አስቸኳይ የህክምና ግብአቶችን እንደሚያቀርቡ አስታውቀዋል።

በዚህ ወሳኝ ጊዜም የቻይና መንግስት ለኢትዮጵያ ላሳየው አጋርነት በጤና ሚኒስቴር እና በራሴ ስም ማመስገን እወዳለሁ ብለዋል።

በተያያዘ ዜና ዶክተር ሊያ ታደሰ አካላዊ ርቀት መጠበቅ እርስ በእርሳችን ከመረዳዳትና በደግነት ከመተሳሰብ ሊያግደን እንደማይገባም አንስተዋል።

የጤና ባለሙያዎች፣ በጤና ተቋማት የሚሰሩ ሰራተኞች፣ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ እና በለይቶ ማቆያ ቆይተው የወጡትን ማግለል ትክክለኛ ያልሆነ ተግባር በመሆኑ መደጋገፍ እንደሚገባ አሳስበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.