Fana: At a Speed of Life!

እንግሊዝ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የህክምና ቁሳቁስ ላከች

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 9 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) እንግሊዝ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የሚረዱ የህክምና ቁሳቁሶችን ልካለች።

የህክምና ቁሳቁሶች ዛሬ አዲስ አበባ የደረሱ ሲሆን፥ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ለኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚሰጡ መሆናቸውን ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የህክምና ቁሳቁሶቹ የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ክፍል ባደረገው የገንዘብ ድጋፍ በዩኒሴፍ ኢትዮጵያ አማካኝነት የተገዙ ናቸው።

የተደረገው ድጋፍ የህክምና ማስክ፣ የቀዶ ጥገና ጋዎኖች፣ የፊት መሸፈኛዎች፣ ሙሉ አካልን የሚሸፍኑ የህክምና አልባሳት እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ያካተተ ነው።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.