Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 4 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 9 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ተጨማሪ 4 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ሚኒስትሯ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ባለፉት 24 ሰአታት ለ842 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 4 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ጠቅሰዋል።

ይህን ተከትሎም በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 96 መድረሱን አስታውቀዋል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ፥ አንደኛው የ22 አመት ወጣት ከዱባይ የመጣና በለይቶ ማቆያ ክትትል ሲደረግለት የቆየ ነው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም የአዲስ አበባ እና የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች የሆኑት የ52 አመት ወንድ እና ሴት ግለሰቦች ቫይረሱ ከተገኘበት ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው ናቸው።

አራተኛዋና የ23 አመቷ ወጣት ደግሞ በአማራ ክልል አዲስ ቅዳም ከተማ ነዋሪ ስትሆን ቫይረሱ ከተገኘበት ሰው ጋር ግንኙነት ስለመኖር አለመኖሩ እየተጣራ ነው።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.