Fana: At a Speed of Life!

ለሁለት ኩባንያዎች የከፍተኛ ደረጃ የደለል ወርቅ ምርት ፈቃድ ተሰጠ

ለሁለት ኩባንያዎች የከፍተኛ ደረጃ የደለል ወርቅ ምርት ፈቃድ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ሚኒስቴር ለሁለት ኩባንያዎች የከፍተኛ ደረጃ የደለል ወርቅ የማምረት ፈቃድ ሰጠ፡፡

ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ስራ ኃ.የተ.የግ.ማ በኢትዮጵያ የተመዘገበና በኢትዮጵያዊያን ባለሀብቶች የተመሰረተ በደለል ወርቅ ምርት ላይ ለመሰማራት ፈቃድ ተሰጥቶታል፡፡

ኩባንያው የምርት ፈቃድ የተሰጠው በጋምቤላ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ ማጃንግ ዞን፣ ማንግሽ ወረዳ ሲሆን÷ ለፕሮጀክቱ ከ138 ሚሊየን 643 ሺህ ብር በላይ መመደቡ ተገልጿል፡፡

የፈቃዱ የአገልግሎት ጊዜው ለአራት ዓመታት እንደሚጸና እና በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ የፋብሪካ ግንባታውን ጨርሶ ወደ ምርት ስራ እንደሚገባ ተመልክቷል፡፡

ሌላው በደለል ወርቅ ምርት ላይ ለመሰማራት ያመለከተውና ፈቃድ የተሰጠው ኩባንያ ኢልኔት ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኃ/የተ/የግል/ማህበር ሲሆን÷ በኢትዮጵያ የተመዘገበና በኢትዮጵያዊያን ባለሀብቶች የተመሰረተ መሆኑ ተጠቁሟል።

ኩባንያው የምርት ፈቃድ የተሰጠው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ አሶሳ ዞን፣ አሶሳ እና ሁዱሉ ወረዳዎች ሲሆን÷ ኩባንያው ለፕሮጀክቱ ከ148 ሚሊየን 225 ሺህ ብር በላይ መመደቡ ተገልጿል፡፡

የፈቃዱ የአገልግሎት ዘመኑ ለአስር ዓመታት መሆኑ እና በሶስት ወራት ውስጥ የፋብሪካ ግንባታውን ጨርሶ ወደ ምርት ይባል መባሉን የማዕድን ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የማዕድን ሚኒስትር ሃብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) እና የኩባንያዎቹ ሥራ አስኪያጆች የፈቃድ ስምምነቱን ተፈራርመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.