Fana: At a Speed of Life!

በስጋ ቤቶች (ሉካንዳዎች) የሚተገበሩ ግዴታዎች

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝም ሆነ ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን ስርጭት ለመከላከል ሲባል በፌደራል ደረጃ አዋጅ መውጣቱ ይታወቃል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዴታዎች መፈፀም የበሽታውን ስርጭት ለመግታት አስተዋፅኦ የሚያደርግ በመሆኑ ሁሉም ስጋ ቤት (ሉካንዳዎች) ለተግባራዊነቱ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ጥሪውን ያስተላልፋል።

ዋና ዋና ግዴታዎች

1. ማንኛውም ስጋ ቤት (ሉካንዳ) ስጋ አስገብቶ ከመሸጡ (አገልግሎት ላይ እንዲውል) ከማድረጉ በፊት ሙሉ ለሙሉ ስጋ ቤቱን እና መጠቀሚያ ቁሳቁሶችን በውሃ ሳሙናና በረኪና በመጠቀም ማጽዳት አለበት፣

2. ማንኛውም ስጋ ቤት (ሉካንዳ) የሚያስገባው ስጋ ህጋዊ እና ከታወቀ ቄራ ታርዶ የቀረበ መሆን አለበት፣

3. ማንኛውም በስጋ ቤት (በሉካንዳ) የሚሰራ ሰራተኛ የስጋ ሽያጭ በሚያከናውንበት ጊዜ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል (ማስክ)፣ ቆብ እና ጋዎን መጠቀም አለበት፣
4. በማንኛውም ስጋ ቤት (ሉካንዳ) ገንዘብ የሚቀበልና ስጋ የሚቆርጥ ሰራተኛ መለየት አለበት፣

5. በማንኛውም ስጋ ቤት (ሉካንዳ) ውስጥ ለሰራተኞች የእጅ ሳሙናና ውሃ ተዘጋጅቶ በየጊዜው እጃቸውን በመታጠብ አገልግሎት መስጠት አለባቸው፣

6. በማንኛውም ስጋ ቤት (ሉካንዳ) ሽያጭ በሚከናወንበት ወቅት ተገልጋዮች ከመሸጫ መስኮቱ 1 (አንድ) ሜትር ርቀው እንዲቆሙና እንዲገለገሉ መደረግ አለበት፣

7. በማንኛውም ስጋ ቤት (ሉካንዳ) ድርጅት ውስጥ የተገልጋይ ቁጥር ከሁለት በላይ በሚሆንበት ወቅት ድርጅቱ ተገልጋዮችን እያንዳንዳቸው ርቀታቸውን በየሁለት እርምጃ ጠብቀው እንዲቆሙና እንዲገለገሉ ማድረግ አለበት፣

8. ከምግብ ቤቶች ጋር የተያያዙ ሉካንዳ ቤቶች ውስጥ ያልበሰለ ስጋ (ቁርጥ/ጥሬ ስጋ፣ ያልበሰለ ክትፎ) ለምግብነት ማቅረብ ለበሽታው ስለሚያጋልጥ የተከለከለ ነው፣

መረጃው የአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት ነው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.