Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች ከዓለም አቀፍ የጥቁር ሕዝቦች ታሪክ፣ ቅርስና  ትምህርት ማዕከል አመራሮች ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በብሪታንያ ከሚኖሩ ዓለም አቀፍ የጥቁር ሕዝቦች ታሪክ፣ ቅርስና ትምህርት ማዕከል አመራሮች ጋር ተወያዩ፡፡

ከንቲባ አዳነች በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ከአመራሮቹ ጋር በአዲስ አበባ የጥቁር ሕዝቦች ታሪክ፣ ቅርስና  ትምህርት ማዕከል መገንባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ፍሬያማ ውይይት ማካሄዳቸውን ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ አፍሪካውያን እና ሌሎች ጥቁር ሕዝቦች ከቅኝ ግዛት ነጻ እንዲወጡ፣ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ወይም የአሁኑ የአፍሪካ ሕብረት  እንዲቋቋም ከፍተኛ ሚና መጫወቷን አስታውሰዋል፡፡

ይህ ታሪክ በየጊዜው የሚታደስ እና በየዘመኑ ቀጣዩ ትውልድ የሚዘክረው በመሆኑ ተቋሙ በመዲናዋ ሊገነባ ላቀደው ማዕከል ከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.