Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 9 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 10፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ምርመራ ከተደረገላቸው 659 ሰዎች መካከል 9 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር ገለጸ።
 
ይህንንም ተከትሎ በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 105 ደርሷል።
 
የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ እንደገለፁት፥ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው መካከል ስምንቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፥ አንዱ የኢኳቶሪያል ጊኒ ዜግነት ያለው ነው።
 
ቫይረሱ ከተገኘባቸው ውስጥም ስድስቱ የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆኑ፥ ሶስቱ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው መሆናቸውን ነው ያመለከቱት።
 
አራቱ ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፥ አንድ የ42 ዓመት ሴት፣ አንድ አንድ የ40 ዓመት ሴት፣ አንድ የ13 ዓመት ወንድ እና አንድ የ73 ዓመት ወንድ ናቸው።
 
ሶስቱ ደግሞ ከጅቡቲ መጥተው በድሬዳዋ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ ሲሆን፥ሁለት የ19 ዓመት ወንዶች እና አንድ የ20 ዓመት ወንድ ናቸው።
 
አንዷ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ከመጀመሩ በፊት ከሊባኖስ የመጣች 20 ዓመት አድሜ ያላት የጅማ ከተማ ነዋሪ ናት።
 
ሚኒስትሯ በእለታዊ መግለጫቸው አንድ ታማሚ ማገገሙን በመግለፅ አንድ ሰው ደግሞ በጽኑ ህሙማን መከታተያ ውስጥ ይገኛል ነው ያሉት።
 
በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ህክምና ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ቁጠር 84 መሆኑንም ሚኒሰትሯ አስታውቀዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.