Fana: At a Speed of Life!

ከተማ አስተዳደሩ ከ71 ሺህ በላይ ለሆኑ ወገኖች ማዕድ አጋራ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዒድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ዛሬ ከ71 ሺህ በላይ በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ወገኖች ማዕድ አጋራ፡፡

የማዕድ ማጋራት ሥነ ስርዓቱ የተከናወነው በከተማዋ የሚገኙ ባለሃብቶችን በማስተባበር መሆኑ ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማዕድ ማጋራት ሥነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ማዕድ ስናጋራ ለወገኖቻችን ፍቅራችንንም ጭምር ነው የምንገልጸው ብለዋል ።

የዒድ አልፈጥርን በዓል ምክንያት በማድረግ 91 የታደሱ ቤቶች ለአቅመ ደካሞችና አረጋውያን እንደሚተላለፉም ጠቁመዋል፡፡

ለማዕድ ማጋራቱ ከ250 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.