Fana: At a Speed of Life!

ለለይቶ ማቆያና ለህክምና ማዕከላት የተዘጋጁ ስፍራዎች ተጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 10፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ለለይቶ ማቆያና ለህክምና ማዕከላት የተዘጋጁ ስፍራዎች ተጎበኙ።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ከተለየዩ አገሮች ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ሰዎች የለይቶ ማቆያ አገልግሎት እየሰጠ ያለውን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አራት ኪሎ ካምፓስን ጎብኝተዋል።

ካምፓሱ በዋናነት ከውጭ አገሮች መጥተው ለአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ በተዘጋጁ ሆቴሎች ለመቆየት አቅም ለሌላቸው ኢትዮጵያውያን አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ ይታወሳል።

የሚኒስትሯ ጉብኝት በዋናነት በካምፓሱ ውስጥ የሚከናወኑ አገልግሎት አሰጣጦች ምን እንደሚመስሉ ለመገምገም መሆኑ ነው የተገለጸው።

በጉብኝታቸውም ከዩኒቨርሲቲው አስተዳደርና በጉዳዩ ከሚሰሩ ሌሎች አካላት ጋር ተወያይተዋል።

አሁን ላይ በካምፓሱ ከተለያዩ አገሮች የመጡ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 321 ሰዎች ያሉ ሲሆን÷ ከእነዚህም ውስጥ 49ኙ ሴቶች መሆናቸውን ኤዚአ ዘግቧል።

በሌላም በኩል በኢፌዴሪ ጤና ሚንስትር ደኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ የሚመራ ቡድን ለለይቶ ማቆያና የህክምና ማዕከላት የተዘጋጁ ስፍራዎችን ጎብኝቷል።

በጉብኝታቸውም ሆስፒታሉ ሙሉ ለሙሉ የኮሮና ቫይረስ ህክምና የሚሰጥበት እንዲሆን መመረጡን ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።

ዶክተር ደረጀ በዚሁ ወቅት ሆስፒታሉ ወረርሽኙን በመከላከል ረገድ አመራሩና የጤና ባለሙያዎች የሚገኙበትን ሁኔታና የህክምና ግብዓቶች ያሉበትን ሁኔታ  መመልከታቸው ተገልጿል።

ቡድኑ ለለይቶ ማቆያና ለህክምና ስፍራ በተዘጋጀባቸው ቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ቲቢ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ ሚሊኒየም አዳራሽ፣ የካቲት 12 ሆስፒታል እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ መሆናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.