Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያ ኩባንያዎች በዲጂታል ኢኮኖሚ መስክ መሳተፍ በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በዲጂታል ኢኮኖሚ መስክ ለመሳተፍ በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ከኢኖቬሽንና  ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር ምክክር አደረጉ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ  ሚኒስትር ዲኤታ ሁሪያ አሊ÷በአፍሪካ አገራት የኢኮኖሚክ ኮሚሽን ሊቀመንበር ኢጎር ሞሮኖዞቭ ከተመራ የሩሲያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ልዑካን ቡድን ጋር ተወያይዋል።

በውይይታቸው የዲጂታል-ኢኮኖሚ ግንባታ ተግባራትን ለማጠናከር እና ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በተለይም የትምህርት ፍትሃዊነትንና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በግሉ ዘርፍ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ የቴክኒክ ኮሚቴ አመራሮች ጋር መክሯል፡፡

የሩሲያ ልዑካን ቡድን አባላት የግል ኩባንያዎች የትምህርት ስርዓትንና እና የኢኮኖሚ ዘርፍን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በማገዝ ረገድ  ሩሲያን ጨምሮ ኡዝቤክስታንና ካዛኪስታን  ሀገራት ላይ ያላቸውን ተሞክሮ አብራርተዋል።

በተለይም ዲጂታል ቴክኖሎጂ በትምህርት ዘርፍ በመጠቀም በጥራትና ተደራሽነት ላይ ያደረጓቸውን ድጋፎች እና የነበሯቸውን ልምዶች  ለማካፈልና አሰራሩን በኢትዮጵያ ለመተግበር ፍላጎት እንዳላቸው መግለፃቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሚኒስትር ደኤታዋ ሁሪያ አሊ በበኩላቸው÷ እስካሁን ከሩሲያ መንግስትና ሕዝብ ጋር  በትምህርት ዘርፍ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በትብብር እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.