Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶቻቸውን ከሱዳን ሊያስወጡ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶቻቸውን ከሱዳን ሊያስወጡ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የሱዳን ጦር መሪ ጀኔራል አብዱል ፈታ አልቡርሃን ዲፕሎማቶቻቸውን ማስወጣት ከሚፈልጉ ሀገራትን አነጋገረዋል፡፡

ጄኔራሉ  አሜሪካ፣ብሪታንያ፣ ቻይና እና ፈረንሳይ ዲፕሎማቶቻቸውን ማስወጣት የሚፈልጉ ሀገራት መሆናቸውን ገልፀው ዲፕሎማቶቹን ከሀገር ለማስወጣት ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል ፡፡

በዋና ከተማዋ ካርቱም የሚገኘው ዋናው የሱዳን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በከባድ መሳሪያዎች ኢላማ በመደረጉ ዲፕሎማቶችን ለማስወጣት የጦር አውሮፕላኖች እንደሚያስፈልጉም ገልፀዋል፡፡

አሜሪካ በበኩሏ ከሱዳን የሚወጡ የኤምባሲ ሰራተኞቿን ለመቀበል ወታደሮቿን ጅቡቲ በሚገኘው የጦር ሰፈሯ እያሰማራች መሆኑን ፔንታጎን አስታውቋል፡፡

በሱዳን ሀይሎቸ መካከል የሚደረገው ጦርነት በአየር፣በምድር እና በከባድ መሳሪያዎች በመታገዝ የቀጠለ ሲሆን÷ በጦርነቱ እስካሁን 400 ሰዎች  ህይወታቸው ማለፉንና በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ መቁሰላቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.