Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከጦር አካል ጉዳተኞች ጋር የትንሳኤ በአልን አከበሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና የካቢኔ አባላት የትንሳኤ በአልን ከጦር አካል ጉዳተኞች ጋር አክብረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የካቤኒ አባሉ ልደታ በሚገኘው የአካል ጉዳተኞች ተሀድሶ ማዕከል በመገኘት ነው በዓሉን ያከበሩት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በእለቱ ባስተላለፉት መልእክት የትንሳኤ በዓልን ለሀገር ባለውለታ ከሆኑት የጦር ጉዳተኞች ጋር በማክበሬ ተደስቻለሁ ብለዋል፡፡

“ትንሳኤ ሌሎችን የምናነሳበትና የምናስታውስበት መሆኑን የምናረጋግጠው በጀግንነት ራሳቸውን ሰጥተው የሀገርን ህልውና ያስቀጠሉ ሰዎች ማስታወስ ስንችል ነው” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

“እናንተም እኛን ከሸኛችሁ በኋላ ከናንተ በላይ በአቅም የደከሙ ሰዎችን በመጠየቅ በፍቅርና በአንድነት ልታከብሩ ይገባል” ነው ያሉት ፡፡

የካቢኔ አባላትም በአሉን በማስመልከት ለማእከሉ የጦር አካል ጉዳተኞች የበግ ስጦታ ማበርከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በማእከሉ የሚገኙ 140 የጦር ጉዳተኞች የጤና እና ሌሎች እንክብካቤዎችን እያገኙ መሆኑ ተጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.