Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የታንዛኒያን የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ለአውሮፓ ገበያ ሊያቀርብ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የታንዛኒያን የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶች በሳምንት ሶስት ቀናት በረራ በማድረግ ለአውሮፓ ገበያ ሊያቀርብ ነው።

አየር መንገዱ የታንዛኒያን የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶች ለአውሮፓ ገበያ እንዲያቀርብ የተደረገው የሀገሪቱ የሆርቲ ካልቼር ማህበር እና የኪሊማንጃሮ ኤርፓርቶች ልማት ኩባንያ ባደረጉት ትብብር ነው።

በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሳምንት ሶስት ቀናት ወደ ኪሊማንጃሮ አውሮፕላን ማረፊያ በመብረር የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶችን ለአውሮፓ ገበያ ያቀርባል ተብሏል።

እንደ ዘ ሲትዝን ዘገባ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አርብ ዕለት በኪሊማንጆሮ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ለአውሮፓ ገበያ የሚቀርበውን የአትክልትና ፍርፍሬ ምርት ሲጭን ነበረ።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ታንዛኒያ ለተለያዩ ሀገራት በምታቀርበው የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶች ላይ አሉታዊ አስተዋዕኦ ማሳረፉ ተነግሯል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድም የሀገሪቱን የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶች ለአውሮፓ ገበያ ማቅረቡ ይህን ተፅዕኖ ያቀለዋል ተብሎ ታምኖበታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.