Fana: At a Speed of Life!

በጋሞ ዞን ትናትና ምሽት ከፍተኛ ዝናብ ባስከተለው ናዳ 5 የቤተሰብ አባላት ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጋሞ ዞን ሳምንቱን እየጣለው ባለው ዝናብ የ8 ሰዎች ህይወት ማለፉን የደቡብ ክልለ አታወቀ።

በጋሞ ዞን ቅዳሜ ምሽት በገረሴ ወረዳ የጣለው ከፍተኛ ዝናብ ባስከተለው ናዳ 5 የቤተሰብ አባላት ህይወት ማለፉ ተጠቁሟል።

በተመሳሳይ ቀን በአርባምንጭ ከተማ ዙሪያም የአንድ ሰው ህይወት በናዳ ማለፉ ነው የተነገረው።

በጨንቻ ዙሪያ ወረዳም ሰሞኑን እየጣለ ያለው ዝናብ ባስከተለው ናዳ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።

በተፈጥሮ አደጋው በሳምንቱ ውስጥ የ 8 ሰዎች ህይወት ማለፉን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

እየጣለ ያለውን ዝናብ ተከትሎ ሌላ ተጨማሪ አደጋ እንዳይከሰት ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበትም የክልሉ መንግስት ጥሪውን ያቀርባል፡፡

በአደጋው ህይወታቸው ላለፈ ዜጎች ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች የክልሉ መንግስት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል።

የመሬት ናዳው ባስከተለው ጉዳት ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉትን የህብረተሰብ ክፍሎች መልሶ ለማቋቋም የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን የሰብአዊ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን አስታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.