Fana: At a Speed of Life!

ጃክ ማ ሶስተኛ ዙር የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ቁሳቁሶችን ለአፍሪካ ሃገራት ሊልኩ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሊባባ ፋውንዴሽን መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ ጃክ ማ ሶስተኛ ዙር የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ቁሳቁሶችን ለአፍሪካ ሃገራት ሊልኩ ነው።

ጃክ ማ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ በርካታ የህክምና ቁሳቁሶችን ለሶስተኛ ጊዜ ለአፍሪካ ሃገራት ሊልኩ መሆኑን አስታውቀዋል።

በዚህም 4 ነጥብ 6 ሚሊየን ማስኮች፣ 500 ሺህ ናሙና መውሰጃ እና መመርመሪያዎች፣ 300 የመተንፈሻ መሳሪያዎች፣ 200 ሺህ አልባሳትና 200 ሺህ የፊት መሸፈኛዎች ለሃገራቱ ይላካሉ።

ከዚህ በተጨማሪም 2 ሺህ የሙቀት ኘመለኪያዎች፣ 100 የሰውነት መለኪያ መሳሪያዎች እንዲሁም 500 ሺህ ጥንድ የእጅ ጓንቶችም የሚላኩ ይሆናል።

ጀክ ማ ከዚህ ቀደም ለአፍሪካ ሃገራት የኮሮና ቫይረስ መከላከያ በሁለት ዙር ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.