Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ሶስት ተጨማሪ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ተጨማሪ ሶስት ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ሚኒስትሯ በ24 ሰአታት ውስጥ ለ396 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ ሶስት ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ብለዋል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ ሁሉም የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ናቸው።

ከዚህ ውስጥ የ11 እና የ15 አመት ታዳጊዎች ከጂቡቲ መጥተው በለይቶ ማቆያ የነበሩ ናቸው ተብሏል።

በተጨማሪም ሶስተኛው ቫይረሱ የተገኘበት የ18 አመቱ ወጣትም በተመሳሳይ መልኩ ከጂቡቲ የመጣና በለይቶ ማቆያ የነበረ ነው።

ይህን ተከትሎም በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 111 ደርሷል።

ከእነዚህ ውስጥ 1 በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ሲገኝ፥ 16 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል ተብሏል።

91 ሰዎች ደግሞ በለይቶ ህክምና ላይ ይገኛሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.