Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ምስጋኑ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንደምትሠራ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላትን ዘመናት የተሻገረ የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንደምትሠራ አምባሳደር ምሥጋኑ አርጋ ገለጹ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምሥጋኑ አርጋ ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላትን ዘመናት የተሻገረ የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንደምትሠራ አምባሳደር ምሥጋኑ መግለጻቸውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያ በማኅበራዊ ልማት እንዲሁም በሠላምና ደኅንነትን ጉዳዮች ላይ ከአሜሪካ ጋር በትብብር ለመሥራት እንደምትፈልግም ነው የገለጹት፡፡

የፕሪቶሪያውን የሠላም ሥምምነት የአተገባበር ሂደት አንስተው በሁለቱ ወገኖች መተማመን ላይ የተመሠረተ እና በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም አስገንዝበዋል፡፡

ቀጣናዊ ጉዳዮችን በተመለከተ እንደገለጹት÷ በሱዳን የተከሰተውን ግጭት ሁለቱ ወገኖች በውይይት ሊፈቱ እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

በሌላ በኩል ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ÷ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ኅብረት ጥላ ሥር የሦስትዮሽ ድርድሩን ለመቀጠል አሁንም እንደወትሮው ሁሉ ዝግጁ መሆኗን ነው በአጽንኦት የገለጹት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሠላም አማራጭ ይዘው ከሸኔ ጋር በታንዛኒያ ለመነጋገር ያሳዩት ተነሳሽነት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሠላም እንዲረጋገጥ ምን ያኅል ጥረት እየተደረገ እንዳለ ማሳያ መሆኑንም ነው ያስረዱት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.