Fana: At a Speed of Life!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በግርማ የሺጥላ ግድያ የተሰማውን ሐዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በግርማ የሺጥላ ግድያ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ፡፡

እኩልነትና ማኅበራዊ ፍትሕ የነገሰባት ጠንካራ ኅብረብሔራዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገው ርብርብ አቶ ግርማ የተሰጣቸውን ታላቅ ሕዝባዊ፣ ድርጅታዊና መንግስታዊ ኃላፊነት በልበሙሉነት፣ በትጋትና በኃላፊነት ስሜት የተወጡ ናቸው ብሏል ምክር ቤቱ፡፡

አቶ ግርማ የሺጥላ÷ ሀገር ወዳድ፣ ብልኅ እና ቁርጠኛ የፖለቲካ አመራር እንደነበሩ ገልጾ÷ ለሀገርና ለወገን ሲሉ ሙሉ ጊዜያቸውን በመጨረሻም የማይተካውን ውድ ሕይወታቸውን ሰውተዋል ብሏል፡፡

የአቶ ግርማ ጉልኅ ሀገራዊና መንግስታዊ አበርክቶ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ ማኅደር ፈፅሞ የሚዘነጋ አይሆንም ነው ያለው ምክር ቤቱ በሐዘን መግለጫው፡፡

ምክር ቤቱ በአቶ ግርማ የሺጥላና በግል ጠባቂዎቻቸው ላይ በደረሰው አደጋ የተሰማውን ሐዘን ገልጾ÷ ለወገኖቻችን ሞት ምክንያት የሆነውንም አሳፋሪ ፅንፈኛ ድርጊትና ጥቃት በፅኑ አውግዟል፡፡

ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለስራ ባልደረቦቻቸውም መፅናናትን ተመኝቷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.